የፋሲካን በአል አስመልክቶ የእሳት አደጋ እዳይፈጠር ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ
02/08/2018
የእሳት አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ እንዲደረግ ስለማሳሰብ ይሆናል
**********************************
የወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ይላል!!
###ማዘጋጃ ቤቱ ሰላማችንን በማስጠበቅና የእሳት አደጋ እንዳይከሰት ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ ህብረተሰቡ በአሉ በሰላም እንዲያሳልፍ በአክብሮት ያሳስባል####
ሌላኛው #ከእሳት አደጋ አስቀድመው በመጠንቀቅ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ያድርጉ
➡️የኤሌክትሪክ ኮንታክት እንዳይፈጠር፣
➡️ሶኬቶች በሙቀጥ እንዳይቃጠሉ፣
➡️የስቶቭ ምድጃዎች ከረጅም ሙቀት የተነሳ እሳት እንዳይፈጥሩ፣
➡️የዲምላይት ገመዶች ኮንታክት አርገው እሳት እንዳያስነሱ፣
➡️የነዳጅ እቃዎች እሳት እንዳይነካቸው ፣
➡️የክብሪት እሳቶች አወዳደቃቸው የሚቀጣጠል ነገሮች ላይ እንዳይወድቁ፣
➡️የሲጋራ ጫፎች ሳታጠፋ እንዳጥሉ፣
➡️የበዓሉ ድምቀት ተብለው የተለኮሱ ሻማዎች ሳይጠፋ እንዳይቆዩ፣
➡️ምጣዶች የሙቀት ሀይል ብዛት እሳት እንዳይፈጥሩ፣
➡️ካፋየር ተብለው እጨቶች ተቀጣጥለው አደገኛ እሳት እንዳያስነሱ.... _ጥንቃቄ እያረጋችሁ በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የጤና ፣ የመቻቻልና የአብሮነት እንዲሆን የወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል።